4 በሰው የርኅራኄ ገመድ፣በፍቅርም ሰንሰለት ሳብኋቸው፤ቀንበሩን ከጫንቃቸው ላይ አነሣሁላቸው፤ዝቅ ብዬም መገብኋቸው።
5 “ታዲያ ንስሓ መግባትን እምቢ በማለታቸው፣ወደ ግብፅ አይመለሱምን?አሦርስ አይገዛቸውምን?
6 በከተሞቻቸው ላይ ሰይፍ ይመዘዛል፤የበሮቻቸውን መወርወሪያ ይቈርጣል፤ስለ ክፉ ዕቅዳቸውም ይደመስሳቸዋል።
7 ሕዝቤ ከእኔ ዘወር ማለትን መረጡ፤ወደ ልዑል ቢጣሩም፣በምንም ዐይነት አያከብራቸውም።
8 “ኤፍሬም ሆይ፤ እንዴት እጥልሃለሁ?እስራኤል ሆይ፤ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ?እንዴት እንደ አዳማ አደርግሃለሁ?እንዴትስ እንደ ሲባዮ እፈጽምብሃለሁ?ልቤ በውስጤ ተናወጠ፤ምሕረቴም ሁሉ ተነሣሥቶአል።
9 የቊጣዬን መቅሠፍት አላመጣም፤ተመልሼም ኤፍሬምን አላጠፋም፤እኔ በመካከላችሁ ያለሁ ቅዱስ አምላክ ነኝ እንጂ፣ሰው አይደለሁምና፣በቊጣ አልመጣም።
10 እግዚአብሔርን ይከተላሉ፤እርሱም እንደ አንበሳ ያገሣል፤እርሱ ሲያገሣ፣ልጆቹ እየተንቀጠቀጡ ከምዕራብ ይመጣሉ።