4 ከመልአኩም ጋር ታገለ፤ አሸነፈውም፤በፊቱ ሞገስን ለማግኘት አልቅሶ ለመነው፣እርሱንም በቤቴል አገኘው፤በዚያም ከእርሱ ጋር ተነጋገረ፤
5 እርሱም ሁሉን የሚገዛ አምላክ እግዚአብሔር፣የሚታወቅበት ስሙም እግዚአብሔር ነው።
6 ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ፍቅርንና ፍትሕን ጠብቅ፤ዘወትርም በአምላክህ ታመን።
7 ነጋዴው በሐሰተኛ ሚዛን ይሸጣል፤ማጭበርበርንም ይወዳል።
8 ኤፍሬም እንዲህ እያለ ይታበያል፤“እኔ ባለጠጋ ነኝ፤ ሀብታምም ሆኛለሁ፤ይህ ሁሉ ሀብት እያለኝ፣ምንም ዐይነት በደል ወይም ኀጢአት አያገኙብኝም።”
9 “ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ፣ አምላካችሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤በዓመት በዓላችሁ ቀን ታደርጉ እንደ ነበረው ሁሉ፣እንደ ገና በድንኳኖች እንድትቀመጡአደርጋችኋለሁ።
10 ለነቢያት ተናገርሁ፤ራእይንም አበዛሁላቸው፤በእነርሱም በኩል በምሳሌ ተናገርሁ።