14 በምድረ በዳ እጅግ መመኘት አበዙ፤በበረሓም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት።
15 እርሱም የለመኑትን ሰጣቸው፤ዳሩ ግን የሚያኰሰምን ሕመም ሰደደባቸው።
16 በሰፈር በሙሴ ላይ፣ ለእግዚአብሔር በተቀደሰውም በአሮን ላይ ቀኑ።
17 ምድር ተከፍታ ዳታንን ዋጠች፤የአቤሮንን ወገን ሰለቀጠች።
18 እሳት በጉባኤያቸው መካከል ነደደ፤ነበልባሉም ክፉዎችን ፈጅቶ አስወገደ።
19 በኮሬብ ጥጃ ሠሩ፤ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ።
20 ክብራቸው የሆነውንም ሣር በሚበላ፣በበሬ ምስል ለወጡ።