1 የምስጋናዬ ምንጭ የሆንህ አምላክ ሆይ፤ ዝም አትበል፤
2 ክፉዎችና አታላዮች፣አፋቸውን ከፍተውብኛልና፤በውሸተኛ አንደበት ተናግረውብኛል።
3 በጥላቻ ቃል ከበውኛል፤ያለ ምክንያትም ጥቃት አድርሰውብኛል።
4 ስወዳቸው ይወነጅሉኛል፤እኔ ግን እጸልያለሁ።
5 በበጎ ፈንታ ክፋትን፣በወደድኋቸው ፈንታ ጥላቻን ይመልሱልኛል።
6 ክፉ ሰው በላዩ ሹም፤ከሳሽም በቀኙ ይቁም።
7 ፍርድ ፊት ሲቆም በደለኛ ሆኖ ይገኝ፤ጸሎቱም ለፍርድ ትሁንበት።