4 ለእስራኤል በተሰጠው ሥርዐት መሠረት፣ የእግዚአብሔርን ስም ለማመስገን፣ የእግዚአብሔር ነገዶች፣ወደዚያ ይመጣሉ።
5 በዚያም የፍርድ ዙፋኖች የሆኑት፣የዳዊት ቤት ዙፋኖች ተዘርግተዋል።
6 እንዲህ ብላችሁ ለኢየሩሳሌም ሰላም ጸልዩ፤“የሚወዱሽ ይለምልሙ፤
7 በቅጥርሽ ውስጥ ሰላም ይሁን፤በምሽግሽም ውስጥ መረጋጋት ይስፈን”።
8 ስለ ወንድሞቼና ስለ ባልንጀሮቼ፣“በውስጥሽ ሰላም ይስፈን” እላለሁ።
9 ስለ አምላካችን ስለ እግዚአብሔር ቤት፣በጎነትሽን እሻለሁ።