7 እርሱ ደመናትን ከምድር ዳርቻ ያስነሣል፤መብረቅ ከዝናብ ጋር እንዲወርድ ያደርጋል፤ነፋሳትንም ከማከማቻው ያወጣል።
8 በኵር ሆኖ በግብፅ የተወለደውን፣ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ቀሠፈ።
9 ግብፅ ሆይ፤ በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ሁሉ ላይ፣በመካከልሽ ታምራትንና ድንቅን ሰደደ።
10 ብዙ ሕዝቦችን መታ፤ኀያላን ነገሥታትንም ገደለ።
11 የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፣የባሳንን ንጉሥ ዐግን፣የከነዓንን ነገሥታት ሁሉ ገደለ፤
12 ምድራቸውንም ርስት አድርጎ፣ለሕዝቡ ርስት እንዲሆን ለእስራኤል ሰጠ።
13 እግዚአብሔር ሆይ፤ ስምህ ዘላለማዊ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ መታሰቢያህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።