8 እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በፊቴ አድርጌአለሁ፤እርሱ በቀኜ ስላለ አልናወጥም።
9 ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ ነፍሴም ሐሤት አደረገች፤ሥጋዬም ያለ ሥጋት ዐርፎ ይቀመጣል፤
10 በሲኦል ውስጥ አትተወኝምና፤ቅዱስህም መበስበስን እንዲያይ አታደርግም።
11 የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣በቀኝህም የዘላለም ፍሥሓ አለ።