1 እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ እባርከዋለሁ፤ምስጋናውም ዘወትር ከአፌ አይለይም።
2 ነፍሴ በእግዚአብሔር ተመካች፤ትሑታንም ይህን ሰምተው ሐሤት ያደርጋሉ።
3 ኑና ከእኔ ጋር እግዚአብሔርን አክብሩት፤ስሙንም በአንድነት ከፍ ከፍ እናድርግ።
4 እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤ እርሱም መለሰልኝ፤ከፍርሀቴም ሁሉ አዳነኝ።
5 ወደ እርሱ የሚመለከቱ ያበራሉ፤ፊታቸውም ከቶ አያፍርም።
6 ይህ ችግረኛ ጮኸ፤ እግዚአብሔርም ሰማው፤ከመከራውም ሁሉ አዳነው።
7 እግዚአብሔርን በሚፈሩት ዙሪያ የእግዚአብሔር መልአክ ይሰፍራል፤ያድናቸዋልም።