8 ከቤትህ ሲሳይ ይመገባሉ፤ከበረከትህም ወንዝ ይጠጣሉ።
9 የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፤በብርሃንህም ብርሃንን እናያለን።
10 ለሚያውቁህ ምሕረትህ፣ልባቸውም ለቀና ጽድቅህ ዘወትር አይቋረጥባቸው።
11 የትዕቢተኛ እግር በላዬ አይምጣ፤የክፉውም ሰው እጅ አያሳደኝ።
12 ክፉ አድራጊዎች እንዴት እንደ ወደቁና እንደ ተጋደሙ፣ቍልቍልም እንደ ተወረወሩና መነሣት እንደማይችሉ ተመልከት!