6 ይዶልታሉ፤ ያደባሉ፤ርምጃዬን ይከታተላሉ፤ነፍሴንም ለማጥፋት ይሻሉ።
7 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከቶ እንዳያመልጡ፣ሕዝቦቹን በቍጣህ ጣላቸው።
8 ሰቆቃዬን መዝግብ፤እንባዬን በዕቃህ አጠራቅም፤ሁሉስ በመዝገብህ የተያዘ አይደለምን?
9 ወደ አንተ በተጣራሁ ቀን፣ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤በዚህም፣ አምላክ ከጐኔ መቆሙን ዐውቃለሁ።
10 ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣ቃሉን በማመሰግነው በእግዚአብሔር፣
11 በአምላክ ታምኛለሁ፤ አልፈራም፤ሥጋ ለባሽ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
12 እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንተ ስእለት አለብኝ፤የማቀርብልህም የምስጋና መሥዋዕት ነው፤