15 ዕድሜው ይርዘም!ከዐረብ ወርቅ ይምጣለት፤ዘወትር ይጸልዩለት፤ቀኑንም ሙሉ ይባርኩት።
16 በምድሪቱ ላይ እህል ይትረፍረፍ፤በተራሮችም ዐናት ላይ ይወዛወዝ።ፍሬው እንደ ሊባኖስ ይንዠርገግ፤በከተማ ያለውም እንደ ሜዳ ሣር እጅብ ብሎ ይውጣ።
17 ስሙ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤ዝናው ፀሓይ የምትኖረውን ዘመን ያህል ይዝለቅ፤ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ይባረኩ፤ሕዝቡ ሁሉ ቡሩክ ነህ ይበለው።
18 ብቻውን ድንቅ ነገር የሚያደርግ፣የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ።
19 ክቡር ስሙ ለዘላለም ይባረክ፤ምድርም ሁሉ በክብሩ ይሞላ።አሜን፤ አሜን።
20 የእሴይ ልጅ የዳዊት ጸሎት እዚህ ላይ ተፈጸመ።