1 መሠረቱን በተቀደሱ ተራሮች አቆመ፤
2 እግዚአብሔር ከያዕቆብ ማደሪያዎች ሁሉ ይልቅ፣የጽዮንን ደጆች ይወዳል።
3 የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፤ስለ አንቺ ክቡር የሆነ ነገር እንዲህ ተብሎ ይነገራል፤ ሴላ
4 “ከሚያውቁኝ መካከል፣ረዓብንና ባቢሎንን እጠቅሳለሁ፤እነሆ፤ ፍልስጥኤምና ጢሮስ ከኢትዮጵያ ጋር፣‘ይህ ሰው በዚያ ነው የተወለደው’ ይላሉ።”