18 በቅድስቲቱ ከተማ ውስጥ የነበሩት የሌዋውያኑ ቍጥር 284 ነበረ።
19 በር ጠባቂዎች፦ዓቁብ፣ ጤልሞንና በሮቹን የሚጠብቁ ወንድሞቻቸው፣ 172 ሰዎች።
20 የቀሩት እስራኤላውያንም ከካህናቱና ከሌዋውያኑ ጋር በይሁዳ ከተሞች ሁሉ በየርስታቸው ተቀመጡ።
21 የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች በዖፌል ኰረብታ ላይ ተቀመጡ፤ ሲሐና ጊሽጳ በእነርሱ ላይ ያዙ ነበር።
22 በኢየሩሳሌም የሌዋውያኑ ዋና አለቃ የሚካ ልጅ፣ የመታንያ ልጅ፣ የሐሻብያ ልጅ፣ የባኒ ልጅ ኦዚ ነበረ፤ ኦዚ በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ለሚዘመረው መዝሙር ኀላፊ ከነበሩት ከአሳፍ ዘሮች አንዱ ነበረ።
23 መዘምራኑ የየዕለቱን ተግባራቸውን በሚቈጣጠረው በንጉሡ ትእዛዝ ሥር ነበሩ።
24 የይሁዳ ልጅ የዛራ ዘር የሆነው የሜሴዜቤል ልጅ ፈታያ ሕዝቡን በሚመለከት ጒዳይ ሁሉ የንጉሡ ተወካይ ነበር።