1 ስለ ራእይ ሸለቆ የተነገረ ንግር፤እስቲ ምን ቢጨንቃችሁ ነው፤ሁላችሁም ሰገነት ላይ የወጣችሁት?
2 አንቺ ጫጫታ የሞላብሽ ከተማ፤የውካታና የፈንጠዝያ ከተማ ሆይ፤የተገደሉብሽ በሰይፍ የተሠዉ አይደሉም፤በጦርነትም አልሞቱም።
3 መሪዎችሽ በሙሉ በአንድ ላይ ሸሽተዋል፤ቀስት እንኳ ሳያነሡ ተማርከዋል፤ጠላት ገና በሩቅ ሳለ የሸሻችሁ ሁሉ፣ተይዛችሁ በአንድነት ታስራችኋል።
4 ስለዚህ፣ “ከእኔ ራቁ፤አምርሬ ላልቅስበት፣ስለ ሕዝቤ ጥፋት፣ልታጽናኑኝ አትሞክሩ” አልሁ።
5 እግዚአብሔር የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርበራእይ ሸለቆ፣የመጯጯኺያ የመረገጥና የሽብር፣ቅጥሮችን የማፈራረስ፣ወደ ተራሮችም የሚጮኽበት ቀን አለው።