10 ከሩብ ጋሻ የወይን ቦታ አንድ የባዶስ መስፈሪያ ያህል የወይን ጭማቂ ብቻ ይገኛል፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ዘር ተዘርቶ አንድ የኢፍ መስፈሪያ እህል ብቻ ይሰጣል።
11 የሚያሰክር መጠጥ ፍለጋማልደው ለሚነሡ፣እስኪያነዳቸውም ወይን በመጠጣትሌሊቱን ለሚያነጉ ወዮላቸ
12 በግብዣቸው ላይ በገናና መሰንቆ፣ከበሮና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤ነገር ግን ለእግዚአብሔር ሥራ ቦታ አልሰጡም፤ለእጆቹም ሥራ ክብር አላሳዩም።
13 ስለዚህ ሕዝቤዕውቀት በማጣቱ ይማረካል፤መኳንንቱም በራብ ይሞታሉ፤ሕዝቡም በውሃ ጥም ይቃጠላል።
14 ስለዚህ ሲኦል ሆዷን አሰፋች፣አፏንም ያለ ልክ ከፈተች፤መኳንንቱና ሕዝቡ ከረብሸኞቻቸውና ከጨፋሪዎቻቸው ጋርወደዚያ ይወርዳሉ።
15 ሰው ይዋረዳል፤የሰው ልጅም ዝቅ ዝቅ ይላል፤የእብሪተኛውም ዐይን ይሰበራል።
16 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግን በፍትሕ ከፍ ከፍ ይላል፤ቅዱሱም አምላክ ቅድስናውን በጽድቅ ይገልጻል።