2 “በእርግጥ ሰው ማለት እናንተ ናኋ!ጥበብም ከእናንተ ጋር ትሞታለቻ!
3 ነገር ግን እኔም እንደ እናንተ አእምሮ አለኝ፤ከእናንተ አላንስም፤እንዲህ ያለውን ነገር የማያውቅ ማን ነው?
4 እግዚአብሔርን ጠርቼ የመለሰልኝ ሰው ብሆንም፣ለባልንጀሮቼ መሣቂያ ሆኛለሁ፤ጻድቅና ያለ ነቀፋ ሆኜ እያለሁ፣ መሣቂያ ሆኛለሁ።
5 የደላቸው በመከራ ያፌዛሉ፤እግሩ የተንሸራተተውንም ይገፈትራሉ።
6 የቀማኞች ድንኳን አይታወክም፤አምላካቸውን በእጃቸው ይዘው እየዞሩም፣እግዚአብሔርንም እያስቈጡ በሰላም ይኖራሉ።
7 “እስቲ እንስሶችን ጠይቁ፤ ያስተምሯችኋል፤የሰማይ ወፎችንም ጠይቁ፣ ይነግሯችኋል፤
8 ለምድር ተናገሩ፤ ታስተምራችኋለች፤የባሕርም ዓሣ ይነግራችኋል።