14 ሰው ከሞተ በኋላ ተመልሶ በሕይወት ይኖራል?እድሳቴ እስከሚመጣ ድረስ፣ተጋድሎ የሞላበትን ዘመኔን ሁሉ እታገሣለሁ።
15 ትጠራኛለህ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤የእጅህንም ሥራ ትናፍቃለህ።
16 በዚያን ጊዜ በእርግጥ እርምጃዬን ትከታተላለህ፤ነገር ግን ኀጢአቴን አትቈጣጠርም።
17 መተላለፌ በከረጢት ይቋጠራል፤ኀጢአቴንም ትሸፍናለህ።
18 “ተራራ እንደሚሸረሸርና እንደሚወድቅ፣ዐለትም ከስፍራው እንደሚወገድ፣
19 ውሃ ድንጋይን እንደሚቦረቡር፣ጐርፍም ዐፈርን አጥቦ እንደሚወስድ፣አንተም የሰውን ተስፋ ታጠፋለህ።
20 አንድ ጊዜ ፈጽመህ ትበረታለህ፤ እርሱም ያልፋል፤ገጽታውን ትቀይራለህ፤ ትሸኘዋለህም።