2 “ሰው እግዚአብሔርን ሊጠቅም ይችላልን?ጠቢብ እንኳ ቢሆን ምን ይጠቅመዋል?
3 አንተ ጻድቅ ብትሆን ሁሉን የሚችለውን አምላክ ምን ደስ ታሰኘዋለህ?መንገድህ ያለ ነቀፋ ቢሆንስ የሚተርፈው ምንድን ነው?
4 “እርሱ የሚገሥጽህ፣ፍርድ ቤትም የሚያቀርብህ ስለምትፈራው ነውን?
5 ክፋትህ ታላቅ፣ኀጢአትህ ፍጻሜ የሌለው አይደለምን?
6 ያለ አንዳች ምክንያት ከወንድሞችህ መያዣ ወስደሃል፤ሰዎችን ገፈህ፣ ያለ ልብስ ዕራቍታቸውን አስቀርተሃል።
7 የዛሉትን ውሃ አላጠጣህም፤የተራቡትንም ምግብ ከልክለሃል።
8 ባለ ርስትና ኀያል፣በእርሱም የምትኖር ክቡር ሰው ብትሆንም፣