17 ድቅድቅ ጨለማ ለሁላቸው እንደ ንጋት ነው፤አሸባሪውን ጨለማ ይወዳጃሉ።
18 “ይሁን እንጂ፣ በውሃ ላይ የሚኵረፈረፍ ዐረፋ ናቸው፤የወይን ቦታው ሰው የማይደርስበት፣ርስታቸው ርጉም ነው።
19 ድርቅና ሙቀት የቀለጠውን በረዶ ከቦታው እንደሚያስወግድ፣ሲኦልም ኀጢአተኞችን ትነጥቃለች።
20 የተሸከመቻቸው ማሕፀን ትረሳቸዋለች፤ትል ይቦጠቡጣቸዋል፤ክፉዎች እንደ ዛፍ ይሰበራሉ፤የሚያስታውሳቸውም የለም።
21 የማትወልደውን መካኒቱን ይቦጠቡጣሉ፤ለመበለቲቱም አይራሩም።
22 ነገር ግን እግዚአብሔር ብርቱዎችን በኀይሉ ጐትቶ ይጥላል፤ቢደላደሉም የሕይወት ዋስትና የላቸውም።
23 ያለ ሥጋት እንዲኖሩ ትቶአቸው ይሆናል፤ዐይኖቹ ግን በመንገዳቸው ላይ ናቸው።