6 ከሜዳ መኖ ይሰበስባሉ፤ከክፉዎች የወይን ቦታም ይቃርማሉ።
7 ዕራቍታቸውን ያለ ልብስ ያድራሉ፤በብርድም ጊዜ የሚለብሱት የላቸውም።
8 ከተራራ በሚወርድ ዝናብ በስብሰዋል፤መጠለያ አጥተው ቋጥኝ ዐቅፈዋል።
9 አባት የሌለው ልጅ ከዕቅፍ ተነጥቋል፤የድኻውም ልጅ በዕዳ ተይዞአል።
10 ዕራቍታቸውን ያለ ልብስ ይሄዳሉ፤ነዶ ይሸከማሉ፤ ግን ይራባሉ።
11 በየተረተሩ የወይራ ዘይት ያወጣሉ፤ወይን እየጠመቁ፣ ለራሳቸው ግን ይጠማሉ፤
12 የሟቾች ጣር ጩኸት ከከተማዋ ይሰማል፤የቈሰሉት ሰዎች ነፍስ ለርዳታ ይጮኻል፤እግዚአብሔር ግን ተጠያቂዎቹን ዝም ብሎአል።