1 “የብር ማዕድን የሚወጣበት፣ወርቅም የሚነጠርበት ስፍራ አለ።
2 ብረት ከመሬት ውስጥ ይገኛል፤መዳብም ከማዕድን ድንጋይ ቀልጦ ይወጣል።
3 ሰው፣ እስከ ጨለማ መጨረሻ ይዘልቃል፤ከድቅድቅ ጨለማ የማዕድን ድንጋይ ለማግኘት፣እስከ ውስጠኛው ዋሻ ገብቶ ይፈልጋል።
4 የሰው እግር ረግጦት በማያውቅበት ስፍራ፣ከሰዎች መኖሪያ ርቆ መውረጃ ጒድጓድ ይቈፍራል፤ሰው በሌለበት ቦታ ይንጠላጠላል፤ ይወዛወዛል።