1 ኤሊሁ በመቀጠል እንዲህ አለ፤
2 “በእግዚአብሔር ፈንታ ሆኜ የምለው አለኝ፤ጥቂት ታገሠኝና እነግርሃለሁ።
3 ዕውቀቴን ከሩቅ አመጣለሁ፤ፈጣሪዬ ጻድቅ እንደሆነ እገልጻለሁ።
4 ቃሌ ሐሰት እንዳልሆነ አረጋግጣለሁ፤በዕውቀቱ ፍጹም የሆነ ሰው ከአንተ ጋር ነው።
5 “እግዚአብሔር ኀያል ነው፤ ግን ማንንም አይንቅም፤ኀያል፣ በዐላማውም ጽኑ ነው።