1 “እስቲ ተጣራ፤ የሚመልስልህ አለን?ከቅዱሳንስ ወደ ማንኛው ዘወር ትላለህ?
2 ሞኙን ሰው ብስጭት ይገድለዋል፤ቂሉንም ቅናት ያጠፋዋል።
3 ቂል ሰው ሥር ሰዶ አየሁት፤ግን ድንገት ቤቱ ተረገመ።
4 ልጆቹ የኑሮ ዋስትና የራቃቸው፤በፍርድ አደባባይ ጥቃት የደረሰባቸው፣ ታዳጊ የሌላቸው ናቸው።
5 ከእሾህ መካከል እንኳ አውጥቶ፤ራብተኛ ሰብሉን ይበላበታል፤ጥማተኛም ሀብቱን ይመኝበታል።
6 ችግር ከምድር አይፈልቅም፤መከራም ከመሬት አይበቅልም።