6 ችግር ከምድር አይፈልቅም፤መከራም ከመሬት አይበቅልም።
7 ፍንጣሪው ከእሳቱ ላይ ሽቅብ እንደሚወረወር፣ሰውም ለመከራ ይወለዳል።
8 “እኔ ብሆን ኖሮ፣ ወደ እግዚአብሔር በቀረብሁ፣ጒዳዬንም በፊቱ በገለጽሁለት ነበር።
9 እርሱ፣ የማይመረመሩ ድንቅ ነገሮች፣የማይቈጠሩም ታምራት ያደርጋል።
10 ምድሪቱን በዝናብ ያረሰርሳል፤ሜዳውንም ውሃ ያጠጣል።
11 የተዋረዱትን በከፍታ ቦታ ያስቀምጣል፤ያዘኑትንም ወደ አስተማማኝ ስፍራ ያወጣቸዋል።
12 እጃቸው ያሰቡትን እንዳይፈጽም፣የተንኰለኞችን ዕቅድ ያከሽፋል።