27 የሀደራም፣ የአውዛል፣ የደቅላ አባት ነበረ፤
28 እንዲሁም የዖባል፣ የአቢማኤል፣ የሳባ፣
29 የኦፊር፣ የኤውላጥ፣ የዮባል አባት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ናቸው።
30 መኖሪያ ስፍራቸውም እስከ ሶፋር ድረስ ይዘልቃል።
31 እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የሴም ዝርያዎች ናቸው።
32 የኖኅ ወንዶች ልጆች ጐሣዎች እንደ ትውልዳቸው በየነገዳቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውሃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ የተሠራጩት ከእነዚሁ ነው።