13 በይሁዳም ከተሞች እጅግ ብዙ ስንቅና ትጥቅ ነበረው። ደግሞም በቂ ልምድ ያላቸውን ተዋጊዎች በኢየሩሳሌም አስቀመጠ።
14 እነርሱም በየቤተ ሰቦቻቸው ሲመዘገቡ እንደሚከተለው ነው፤ ከይሁዳ የየሻለቃው አዛዦች፣ አዛዡ ዓድና ከሦስት መቶ ሺ ተዋጊዎች ጋር፤
15 ከእርሱ ቀጥሎም አዛዡ የሆሐናን ከሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ጋር፤
16 ከዚያ ቀጥሎም ለእግዚአብሔር አገልግሎት በፈቃደኝነት ራሱን የሰጠው የዝክሪ ልጅ ዓማስያ ከሁለት መቶ ሺህ ተዋጊዎች ጋር፤
17 ከብንያምም ጀግናው ወታደር ኤሊዳሄ ቀስትና ጋሻ ከያዙ ከሁለት መቶ ሺ ሰዎች ጋር፤
18 ቀጥሎም ዮዛባት ለጦርነት ዝግጁ ከሆኑ ከአንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ሰዎች ጋር፤
19 እነዚህ እንግዲህ በመላው ይሁዳ በተመሸጉት ከተሞች ካስቀመጣቸው ሌላ፣ ንጉሡን ያገለግሉ የነበሩ ሰዎች ናቸው።