1 ኤፍሬም የነፋስ እረኛ ነው፤ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል፤ሐሰትንና ዐመፅን ያበዛል።ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋል፤የወይራ ዘይትንም ወደ ግብፅ ይልካል።
2 እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ የሚያቀርበው ክስ አለው፤ያዕቆብን እንደ መንገዱ ይቀጣዋል፤እንደ ሥራውም ይከፍለዋል።
3 በማሕፀን ሳለ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፤ሙሉ ሰውም ሲሆን ከአምላክ ጋር ታገለ።
4 ከመልአኩም ጋር ታገለ፤ አሸነፈውም፤በፊቱ ሞገስን ለማግኘት አልቅሶ ለመነው፣እርሱንም በቤቴል አገኘው፤በዚያም ከእርሱ ጋር ተነጋገረ፤