2 “የሰው ልጅ ሆይ፤ ስለ ጢሮስ ሙሾ አውርድ፤
3 በባሕር መግቢያ ላይ ለምትገኘውና በብዙ ጠረፎች ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር ለምትነግደው ለጢሮስ እንዲህ በላት፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ጢሮስ ሆይ!፤“ፍጹም ውብ ነኝ” ብለሻል፤
4 ዳርቻሽ በባሕር መካከል ነው፤ሠሪዎችሽም ፍጹም ውብ አድርገውሻል።
5 ሳንቃዎችሽን ሁሉ፣ከሳኔር በመጣ ጥድ ሠሩ፤ደቀልንም ይሠሩልሽ ዘንድ፤ከሊባኖስ ዝግባ አመጡ።
6 ከባሳን በመጣ ወርካ፣መቅዘፊያሽን ሠሩ፤ከቆጵሮስ ጠረፍ በመጣ ዝግባ፣በዝኆን ጥርስ ለብጠው ወለልሽን ሠሩ።
7 የመርከቦችሽ ሸራ ጥልፍ ሥራ ያለበት የግብፅ በፍታ ነበረ፤ይህም እንደ ዐርማ አገለገለሽ።መጋረጃዎችሽ ከኤሊሳ ጠረፍ የመጡ፣ባለ ሰማያዊና ሐምራዊ ቀለም ነበሩ።
8 ቀዛፊዎችሽ ከሲዶናና ከአራድ የመጡ ነበሩ፤ጢሮስ ሆይ፤ የራስሽ ጠቢባን የመርከቦችሽ መሪዎች ነበሩ።