2 ሰባኪው፣“ከንቱ፣ ከንቱ፣የከንቱ ከንቱ፤ሁሉም ነገር ከንቱ ነው” ይላል።
3 ከፀሓይ በታች ከሚለፋበት ተግባር ሁሉ፣ሰው ምን ትርፍ ያገኛል?
4 ትውልድ ይሄዳል፤ ትውልድ ይመጣል፤ምድር ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።
5 ፀሓይ ትወጣለች፤ ትጠልቃለችም፤ወደምትወጣበትም ለመመለስ ትጣደፋለች።
6 ነፋስ ወደ ደቡብ ይነፍሳል፤ወደ ሰሜንም ይመለሳል፤ዞሮ ዞሮ ይሄዳል፤ዘወትርም ወደ ዑደቱ ይመለሳል።
7 ወንዞች ሁሉ ወደ ባሕር ይፈሳሉ፤ባሕሩ ግን ፈጽሞ አይሞላም፤ወንዞች ወደ መጡበት ስፍራ፣ወደዚያ እንደ ገና ይመለሳሉ።
8 ሰው መናገር ከሚችለው በላይ፣ነገሮች ሁሉ አድካሚ ናቸው፤ዐይን ከማየት አይጠግብም፤ጆሮም በመስማት አይሞላም።