9 ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው፤በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እወረውራለሁ፤በፍልስጥኤም ላይ በድል አድራጊነት እፎክራለሁ።”
10 ወደ ተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል?ወደ ኤዶምያስስ ማን ያደርሰኛል?
11 እግዚአብሔር ሆይ፤ የጣልኸን አንተ አይደለህምን?አምላክ ሆይ፤ ከሰራዊታችንም ጋር አልወጣ አልህ!
12 አሁንም የሰው ማዳን ከንቱ ነውና፣በጠላታችን ላይ ድልን አቀዳጀን።
13 እግዚአብሔር ሲረዳን ብርቱ እንሆናለን፤ጠላቶቻችንንም ከእግሩ በታች የሚረግጥ እርሱ ነው።