2 አገር ስታምፅ፣ ገዦቿ ይበዛሉ፤አስተዋይና ዐዋቂ ሰው ግን ሥርዐትን ያሰፍናል።
3 ድኾችን የሚያስጨንቅ ሰው፣ሰብል እንደሚያጠፋ ኀይለኛ ዝናብ ነው።
4 ሕግን የሚተዉ ክፉዎችን ያወድሳሉ፤ሕግን የሚጠብቁ ግን ይቋቋሟቸዋል።
5 ክፉዎች ፍትሕን አያስተውሉም፤ እግዚአብሔርን የሚሹ ግን ሙሉ በሙሉ ያውቁታል።
6 በአካሄዱ ነውር የሌለበት ድኻ፣መንገዱ ጠማማ ከሆነ ባለጠጋ ይሻላል።
7 ሕግን የሚጠብቅ አስተዋይ ልጅ ነው፤ከሆዳሞች ጋር ጓደኛ የሚሆን ግን አባቱን ያዋርዳል።
8 በከፍተኛ ወለድ ሀብቱን የሚያካብት፣ለድኻ ለሚራራ፣ ለሌላው ሰው ያከማችለታል።