1 ኑኃሚን፤ ከአቤሜሌክ ጐሣ የሆነ ቦዔዝ የሚባል ባለጸጋ የባል ዘመድ ነበራት።
2 ሞዓባዊቷ ሩትም ኑኃሚንን፣ “በፊቱ ሞገስ አግኝቼ ቃርሚያ የሚያስቃርመኝ ሰው ባገኝ እስቲ ወደ እህል አዝመራው ልሂድ” አለቻት።ኑኃሚንም፣ “ልጄ ሆይ፤ ይሁን ሂጂ” አለቻት።
3 ስለዚህ እርሷም ወጣች፤ ከአጫጆች ኋላ ኋላ እየተከታተለችም ከአዝመራው ቦታ ትቃርም ጀመር፤ እንዳጋጣሚ ትቃርምበት የነበረው አዝመራ ከአቤሜሌክ ጐሣ የሆነው የቦዔዝ ነበር።
4 በዚሁ ጊዜ ቦዔዝ ከቤተ ልሔም መጣ፤ አጫጆቹንም፣ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን” ብሎ ሰላምታ ሰጣቸው።እነርሱም፣ “እግዚአብሔር ይባርክህ” ብለው መለሱለት።
5 ከዚያም ቦዔዝ የአጫጆቹን አለቃ፣ “ይህች ወጣት ሴት የማን ናት?” ሲል ጠየቀው።
6 የአጫጆቹም አለቃ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ከኑኃሚን ጋር ከሞዓብ ምድር ተመልሳ የመጣች ሞዓባዊት ናት።