12 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “በተራራው ላይ ወደ እኔ ና፤ በዚህም ቆይ፤ እኔም መመሪያ እንዲሆናቸው ሕግና ትእዛዛት የጻፍኩባቸውን የድንጋይ ጽላቶች እሰጥሃለሁ” አለው።
13 ከዚያም ሙሴ ከረዳቱ ከኢያሱ ጋር አብሮ ሄደ፤ ሙሴም ወደ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ተራራ ወጣ።
14 እርሱም ሽማግሌዎችን “ወደ እናንተ እስክንመለስ ድረስ በዚህ ቆዩ፤ አሮንና ሖር ከእናንተ ጋር ናቸው፤ ክርክር ያለው ሰው ቢኖር ወደ እነርሱ ይሂድ።” አላቸው።
15 ሙሴ ወደ ተራራ ሲወጣ ደመናው ተራራውን ሸፈነ፤
16 የእግዚአብሔርም (ያህዌ) ክብር በሲና ተራራ ላይ ወረደ፣ ደመናውም ተራራውን እስከ ስድስት ቀን ድረስ ሸፈነው፤ በሰባተኛውም ቀን እግዚአብሔር (ያህዌ) በደመናው ውስጥ ሆኖ ሙሴን ጠራው።
17 ለእስራኤላውያን የእግዚአብሔር (ያህዌ) ክብር በተራራው ጫፍ ላይ እንደሚባላ እሳት ሆኖ ይታይ ነበር
18 ከዚያም ሙሴ ወደ ተራራው ሲወጣ ደመናው ውስጥ ገባ፤ በተራራውም ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቆየ።