3 “ጌታ ሆይ፤ ነቢያትህን ገድለዋል፤ መሠዊያዎችህን አፍርሰዋል፤ እኔም ብቻዬን ቀረሁ፤ ሊገድሉኝም ይፈልጋሉ።”
4 እግዚአብሔር የሰጠው መልስ ግን ምን ነበር? “ለበኣል ያልሰገዱትን ሰባት ሺህ ሰዎች ለራሴ አስቀርቻለሁ።”
5 በአሁኑ ጊዜም እንደዚሁ በጸጋ የተመረጡ ትሩፋን አሉ።
6 እንግዲህ በጸጋ ከሆነ በሥራ አይደለም፤ በሥራ ቢሆንማ ኖሮ ጸጋ፣ ጸጋ መሆኑ በቀረ ነበር።
7 እንግዲህ ምንድን ነው? እስራኤል አጥብቀው የፈለጉትን አላገኙትም፤ የተመረጡት ግን አገኙት፤ የቀሩትም ልባቸው ደነደነ፤
8 እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤“ዐይናቸው እንዳያይ፣ጆሮአቸውም እንዳይሰማ፣እግዚአብሔር እስከዚህ ቀን ድረስ፣የድንዛዜ መንፈስ ሰጣቸው።”
9 ዳዊትም አለ፤“ማእዳቸው አሽክላና ወጥመድ፣ዕንቅፋትና ቅጣት ይሁንባቸው።