20 ኑኃሚንም ምራቷን፣ “በጎነቱን ለሕያዋንም ሆነ ለሙታን ማድረጉን ያልተወ እግዚአብሔር ይባርከው” አለቻት፤ ቀጥላም፣ “ሰውየው እኮ የሥጋ ዘመዳችን ነው፤ የመቤዠት ግዴታ ካለባቸው ዘመዶቻችን አንዱ እርሱ ነው” አለቻት።
21 ከዚያም ሞዓባዊቷ ሩት፣ “ደግሞም፣ ‘እህሌን ሁሉ አጭደው እስኪጨርሱ ድረስ ከሠራተኞቼ አትለዪ! ብሎኛል” አለቻት።
22 ኑኃሚንም ምራቷን ሩትን፣ “የኔ ልጅ፤ እንዲህ ካልሽማ ከሴት ሠራተኞቹ ጋር አብሮ መሄድ ይሻልሻል፤ ወደ ሌላ ሰው አዝመራ ብትሄጂ ጒዳት ሊያገኝሽ ይችላልና” አለቻት።
23 ስለዚህ የገብሱና የስንዴው አዝመራ ተሰብስቦ እስኪያበቃ ድረስ፣ ሩት የቦዔዝን ሴቶች ሠራተኞች ተጠግታ ቃረመች፣ ከአማቷም ጋር ኖረች።