15 እንዲሁም፣ “በላይሽ የደረብሽውን ልብስ አቅርቢልኝ፤ ዘርግተሽም ያዢው” አላት፤ ዘርግታ እንደ ያዘችም፤ ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰፍሮ አሸከማት፤ ከዚያም ወደ ከተማ ተመለሰች።
16 ሩት ወደ አማቷ እንደ ተመለሰች፣ ኑኃሚን፣ “ልጄ ሆይ፤ የሄድሽበት ጒዳይ እንዴት ሆነ?” ብላ ጠየቀቻት።ሩትም ቦዔዝ ያደረገላትን ሁሉ ነገረቻት፤
17 ቀጥላም፣ “ ‘ወደ አማትሽ ባዶ እጅሽን አትመለሺ’ በማለት ይህን ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰጠኝ” አለቻት።
18 ኑኃሚንም፣ “ልጄ ሆይ፤ የሚሆነውን ነገር እስክታውቂ ድረስ ታገሺ፤ ጒዳዩ ዛሬውኑ እልባት ካላገኘ ሰውየው አያርፍም” አለቻት።