48 የእንባ ጐርፍ ከዐይኔ ፈሰሰ፤ሕዝቤ አልቋልና።
49 ያለ ዕረፍት፣ያለ ማቋረጥ ዐይኖቼ እንባ ያፈሳሉ፤
50 እግዚአብሔር ከላይ፣ከሰማይ እስኪያይ ድረስ።
51 በከተማዬ ባሉት ሴቶች ሁሉ ላይ የደረሰውን ማየቴ፣ነፍሴን አስጨነቃት።
52 ያለ ምክንያት ጠላቶቼ የሆኑ፣እንደ ወፍ አደኑኝ።
53 ሕይወቴን በጒድጓድ ውስጥ ሊያጠፉ ሞከሩ፣ድንጋይም በላዬ አደረጉ።
54 ውሃ ሞልቶ በዐናቴ ላይ ፈሰሰ፤ጠፍቻለሁ ብዬ አሰብሁ።