1 ለደም ከተማ ወዮላት!ሐሰት፣ዘረፋም ሞልቶባታል፤ብዝበዛዋ ተግዞ አያልቅም።
2 የጅራፍ ድምፅ፣የመንኰራኵር ኳኳቴ፣የፈጣን ፈረስ ኮቴ፣የሠረገሎች ድምፅ ተሰምቶአል
3 ፈረሰኛው ይጋልባል፤ሰይፍ ይንቦገቦጋል፤ጦር ያብረቀርቃል፤የሞተው ብዙ ነው፤ሬሳ በሬሳ ሆኖአል፤ስፍር ቍጥር የለውም፤መተላለፊያ አልተገኘም።
4 ይህ ሁሉ የሆነው ቅጥ ባጣች፣አሳሳችና መተተኛ በሆነች ዘማዊት ምክንያት ነው፤እርሷም በዝሙቷ አሕዛብን፣በጥንቈላዋም ሕዝቦችን ባሪያ ያደረገች ናት።