9 ኢትዮጵያና ግብፅ ወሰን የለሽ ኀይሏ ናቸው፤ፉጥና ሊቢያም ረዳቶቿ ነበሩ።
10 ይሁን እንጂ በምርኮ ተወሰደች፤ተሰዳም ሄደች።በየመንገዱ ማእዘን ላይ፣ሕፃናቷ ተፈጠፈጡ፤በመሳፍንቷ ላይ ዕጣ ተጣለ፤ታላላቅ ሰዎቿ ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ።
11 አንቺ ደግሞ ትሰክሪያለሽ፤ትደበቂያለሽ፣ከጠላትም መሸሸጊያ ትፈልጊያለሽ።
12 ምሽጎችሽ ሁሉ ሊበሉ እንደ ደረሱየመጀመሪያ በለስ ፍሬ ናቸው፤በሚወዛወዙበት ጊዜ፣ፍሬዎቹ በበላተኛው አፍ ውስጥ ይወድቃሉ።
13 እነሆ፤ ጭፍሮችሽ፣ሁሉም ሴቶች ናቸው!የምድርሽ በሮች፣ለጠላቶችሽ ወለል ብለው ተከፍተዋል፤መዝጊያዎቻቸውንም እሳት በልቶአቸዋል።
14 ለከበባው ውሃ ቅጂ፤መከላከያሽን አጠናክሪ፤የሸክላውን ዐፈር ፈልጊ፤ጭቃውን ርገጪ፤ጡቡንም ሥሪ።
15 በዚያ እሳት ይበላሻል፤ሰይፍ ይቈርጥሻል፤እንደ ኵብኵባም ይግጥሻል።እንደ ኵብኵባ እርቢ፤እንደ አንበጣም ተባዢ።