2 “እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ማንም የለም፤ከአንተም በቀር ሌላ የለም፤እንደ አምላካችን ያለ ዐለት የለም።
3 “ይህን ያህል በመታበይ አትናገሩ፤እንዲህ ያለውም የእብሪት ቃል ከአፋችሁ አይውጣ፤ እግዚአብሔር አምላክ ዐዋቂ ነውና፤ሥራም ሁሉ በእርሱ ይመዘናል።
4 “የኀያላን ቀስቶች ተሰባብረዋል፤ደካሞች ግን በኀይል ታጥቀዋል።
5 ጠግበው የነበሩ ለእንጀራ ሲሉ ተገዙ፤ተርበው የነበሩ ግን እንጀራ ጠገቡ፤መካኒቱ ሰባት ልጆች ወልዳለች፤ብዙ ወንዶች ልጆች ወልዳ የነበረችው ግን መከነች።
6 “እግዚአብሔር ይገድላል፤ ያድናልም፤ወደ መቃብር ያወርዳል፤ ያወጣልም።
7 እግዚአብሔር ያደኸያል፤ ያበለጽጋልም፤ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍም ያደርጋል።
8 እርሱ ድኻውን ከትቢያ ያነሣል፤ምስኪኑንም ከጒድፍ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ከመኳንንቱ ጋር ያስቀምጣቸዋል፤የክብር ዙፋንም ያወርሳቸዋል።“የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፣ዓለምን በእነርሱ ላይ አድርጎአል።