1 ሽማግሌው፤በእውነት ለምወደው ለውድ ወዳጄ፣ ለጋይዮስ፤
2 ወዳጅ ሆይ፤ ነፍስህ በመልካም ሁኔታ ላይ እንዳለች ሁሉ መልካም ጤንነት እንዲኖርህና በነገር ሁሉ እንዲሳካልህ እጸልያለሁ።
3 ለእውነት ታማኝ እንደሆንህና የምትመላለሰውም በእውነት እንደሆነ አንዳንድ ወንድሞች መጥተው ስለ አንተ ሲመሰክሩልኝ እጅግ ደስ አለኝ።
4 ልጆቼ በእውነት የሚመላለሱ መሆናቸውን ከመስማት የሚበልጥ ደስታ የለኝም።
5 ወዳጅ ሆይ፤ ለአንተ እንግዶች ቢሆኑም እንኳ ለወንድሞች በምታደርገው ነገር ሁሉ ታማኝ ነህ።
6 እነርሱ አንተ ስላለህ ፍቅር በቤተ ክርስቲያን ፊት መስክረዋል፤ በመንገዳቸውም እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ ብትረዳቸው መልካም ታደርጋለህ፤