1 ዳዊት ከሳኦል ጋር የሚያደርገውን ንግግር እንዳበቃ፤ የዮናታን ነፍስ ከዳዊት ነፍስ ጋር ተቈራኘች፤ እንደራሱም አድርጎ ወደደው።
2 ከዚያች ዕለት አንሥቶ ሳኦል ዳዊትን አብሮት እንዲኖር አደረገ፤ ወደ አባቱም ቤት እንዲመለስ አላሰናበተውም።
3 ዮናታን እንደ ራሱ አድርጎ ስለ ወደደው፣ ከዳዊት ጋር ኪዳን አደረገ፤
4 ዮናታን የለበሰውን ካባ አውልቆ ከነጦር ልብሱ፣ በተጨማሪም ሰይፉን፣ ቀስቱንና መታጠቂያውን ሰጠው።