1 ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፤“ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፤ቀንዴም በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤በማዳንህ ደስ ይለኛልና።
2 “እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ማንም የለም፤ከአንተም በቀር ሌላ የለም፤እንደ አምላካችን ያለ ዐለት የለም።
3 “ይህን ያህል በመታበይ አትናገሩ፤እንዲህ ያለውም የእብሪት ቃል ከአፋችሁ አይውጣ፤ እግዚአብሔር አምላክ ዐዋቂ ነውና፤ሥራም ሁሉ በእርሱ ይመዘናል።
4 “የኀያላን ቀስቶች ተሰባብረዋል፤ደካሞች ግን በኀይል ታጥቀዋል።