4 “የኀያላን ቀስቶች ተሰባብረዋል፤ደካሞች ግን በኀይል ታጥቀዋል።
5 ጠግበው የነበሩ ለእንጀራ ሲሉ ተገዙ፤ተርበው የነበሩ ግን እንጀራ ጠገቡ፤መካኒቱ ሰባት ልጆች ወልዳለች፤ብዙ ወንዶች ልጆች ወልዳ የነበረችው ግን መከነች።
6 “እግዚአብሔር ይገድላል፤ ያድናልም፤ወደ መቃብር ያወርዳል፤ ያወጣልም።
7 እግዚአብሔር ያደኸያል፤ ያበለጽጋልም፤ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍም ያደርጋል።
8 እርሱ ድኻውን ከትቢያ ያነሣል፤ምስኪኑንም ከጒድፍ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ከመኳንንቱ ጋር ያስቀምጣቸዋል፤የክብር ዙፋንም ያወርሳቸዋል።“የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፣ዓለምን በእነርሱ ላይ አድርጎአል።
9 እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል፤ክፉዎች ግን በጨለማ ውስጥ ይጣላሉ፤“ሰው በኀይሉ ድል አያደርግም፤
10 ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቃሉ፤እርሱ ከሰማይ ያንጐደጒድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል።“ለንጉሡ ኀይልን ይሰጣል፤የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”