1 ሳሙኤል 23:3-9 NASV

3 የዳዊት ሰዎች ግን፣ “እዚሁ በይሁዳ ምድር እያለን እየፈራን ነው፤ የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ለመውጋት ወደ ቅዒላ የምንሄድ ከሆነማ ምን ያህል የሚያስፈራ ነው?” አሉት።

4 ዳዊት እንደ ገና እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፣ “ፍልስጥኤማውያንን በእጅህ አሳልፌ ስለምሰጥ፣ ወደ ቅዒላ ውረድ” አለው።

5 ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ቅዒላ ሄደው፣ ፍልስጥኤማውያንን ወጉ፤ እንስሶቻቸውን ማርከው ወሰዱ፤ በፍልስጥኤማውያን ላይ ከባድ ጒዳት አደረሱ፤ ዳዊትም የቅዒላን ሕዝብ ታደገ።

6 የአቢሜሌክ ልጅ አብያታር ወደ ቅዒላ ወደ ዳዊት በሸሸ ጊዜ፣ ኤፉዱን ይዞ ወርዶ ነበር።

7 ሳኦል የዳዊትን ወደ ቅዒላ መሄድ በሰማ ጊዜ፣ “ዳዊት መዝጊያና የብረት መወርወሪያ ወዳላት ከተማ መግባቱ፣ ራሱን በራሱ እንደ ማሰር ስለ ሆነ፣ ይህን ሰው እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኛል” አለ።

8 ሳኦልም፣ ወደ ቅዒላ ወርደው ዳዊትንና ሰዎቹን እንዲከቡ፣ ሰራዊቱን በሙሉ ለጦርነት ጠራ።

9 ዳዊትም ሳኦል ክፉ እንዳሰበበት ባወቀ ጊዜ፣ ካህኑን አብያታርን፣ “ኤፉዱን አምጣ” አለው።