1 ሳሙኤል 29:1-5 NASV

1 ፍልስጥኤማውያን ሰራዊታቸውን ሁሉ በአፌቅ ሰበሰቡ፤ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል ሸለቆ ባለው ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ፤

2 የፍልስጥኤማውያን ገዦች በመቶና በሺህ ሆነው ሲዘምቱ፣ ዳዊትና ሰዎቹም ከአንኩስ ጋር ደጀን ሆነው ይከተሉ ነበር።

3 የፍልስጥኤም አዛዦችም፣ “እነዚህ ዕብራውያን እዚህ ምን እያደረጉ ነው?” ብለው ጠየቁ።አንኩስም፣ “ይህ የእስራኤል ንጉሥ የሳኦል አገልጋይ የነበረው ዳዊት አይደለምን?” ከእኔ ጋር መኖር ከጀመረ እነሆ ዓመት አለፈው፤ እኔን ከተጠጋበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ምንም በደል አላገኘሁበትም” አላቸው።

4 የፍልስጥኤማውያን አዛዦች ግን በአንኩስ ላይ ተቈጥተው እንዲህ አሉ፤ “ይህን ሰው ወደዚያው ወደ ሰጠኸው ቦታ ይመለስ ዘንድ ስደደው፤ በውጊያው ጊዜ በእኛ ላይ ተመልሶ ጠላት እንዳይሆን፣ አብሮን ወደ ጦርነቱ መሄድ የለበትም፤ የእኛን ሰዎች ራስ ቈርጦ ካልወሰደ ከጌታው ጋር እንዴት ሊታረቅ ይችላል?

5 በዘፈን እየተቀባበሉ፣‘ሳኦል ሺህ ገደለ፤ ዳዊት ግን ዐሥር ሺህ’ብለው የዘመሩለት ይኸው ዳዊት አይደለምን?”