3 ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ጺቅላግ እንደ ደረሱም፣ እነሆ፤ ከተማዪቱ በእሳት ጋይታ፣ ሚስቶቻቸው፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ተማርከው አገኙ።
4 በዚህ ጊዜ ዳዊትና ሰዎቹ ማልቀስ እስከሚያቅታቸው ድረስ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤
5 ሁለቱ የዳዊት ሚስቶች ማለትም ኢይዝራኤላዊቷ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቢግያም ተማርከው ነበር።
6 ሰዎቹ ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ነፍሳቸው ተመራ ሊወግሩት ስለ ተመካከሩ ዳዊት በጣም ተጨነቀ፤ ነገር ግን ዳዊት በአምላኩ በእግዚአብሔር በረታ።
7 ከዚያም ዳዊት የአቢሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን፣ “ኤፉዱን አምጣልኝ” አለው፤ አብያታርም አመጣለት፤
8 ዳዊትም፣ “ይህን ወራሪ ሰራዊት ልከተለውን?’ እደርስባቸዋለሁን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፣ “በእርግጥ ትደርስባቸዋለህ፤ ምርኮውንም ትመልሳለህ፤ ተከተል” ሲል መለሰለት።
9 ስለዚህ ዳዊትና አብረውት የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ወደ ቦሦር ወንዝ መጡ፤ ጥቂቶቹም በቦሦር ወንዝ ቈዩ፤