1 በሕዝብ ተሞልታ የነበረችው ከተማ፣እንዴት የተተወች ሆና ቀረች!በሕዝቦች መካከል ታላቅ የነበረችው፣እርሷ እንዴት እንደ መበለት ሆነች!በአውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረችው፣አሁን ባሪያ ሆናለች።
2 በሌሊት አምርራ ታለቅሳለች፤እንባዋ በጉንጮቿ ላይ ይወርዳል፤ከወዳጆቿ ሁሉ መካከል፣የሚያጽናናት ማንም የለም፤ባልንጀሮቿ ሁሉ ከድተዋታል፤ጠላቶቿም ሆነዋል።
3 በመከራና በመረገጥ ብዛትይሁዳ ተማርካ ሄደች፤በሕዝቦችም መካከል ተቀመጠች፤የምታርፍበትንም ስፍራ አጣች፤በጭንቀቷ መካከል ሳለች፣አሳዳጆቿ ሁሉ አገኟት።
4 የጽዮን መንገዶች ያለቅሳሉ፤በዓላቷን ለማክበር የሚመጣ የለምና፤በበሮቿ ሁሉ የሚገባና የሚወጣ የለም፤ካህናቷ ይቃትታሉ፤ደናግሏ ክፉኛ አዝነዋል፤እርሷም በምሬት ትሠቃያለች።