4 እርሱ ሥጋዬንና ቈዳዬን አስረጀ፤ዐጥንቶቼንም ሰባበረ።
5 በምሬትና በድካም፣ቅጥር ሠራብኝ፤ ዙሪያዬንም ከበበኝ።
6 ከሞቱ ብዙ ጊዜ እንደሆናቸው፣በጨለማ እንድኖር አደረገኝ።
7 በቅጥር ውስጥ ዘጋብኝ፤ ስለዚህ ማምለጥ አልቻልሁም፤የእስር ሰንሰለቴንም አከበደብኝ።
8 ርዳታ ፈልጌ ብጣራና ብጮኽ እንኳ፣ጸሎቴን መስማት አልፈለገም።
9 መንገዴን በተጠረቡ ድንጋዮች ዘጋ፤ጐዳናዬንም አጣመመ።
10 አሸምቆ እንደ ተኛ ድብ፣እንደ አደባም አንበሳ፣