50 እግዚአብሔር ከላይ፣ከሰማይ እስኪያይ ድረስ።
51 በከተማዬ ባሉት ሴቶች ሁሉ ላይ የደረሰውን ማየቴ፣ነፍሴን አስጨነቃት።
52 ያለ ምክንያት ጠላቶቼ የሆኑ፣እንደ ወፍ አደኑኝ።
53 ሕይወቴን በጒድጓድ ውስጥ ሊያጠፉ ሞከሩ፣ድንጋይም በላዬ አደረጉ።
54 ውሃ ሞልቶ በዐናቴ ላይ ፈሰሰ፤ጠፍቻለሁ ብዬ አሰብሁ።
55 በጥልቁ ጒድጓድ ውስጥ ሳለሁ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንተን ስም ጠራሁ።
56 ልመናዬን ሰምተሃል፤ “ርዳታም ፈልጌ ስጮኽ፣ከመስማት ጆሮህን አትከልክል።”